3 እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤መልካም ነውና፣ ለስሙ ዘምሩ፤
4 እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፣እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጦአልና።
5 እግዚአብሔር ታላቅ እንደሆነ፣ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።
6 በሰማይና በምድር፣በባሕርና በጥልቅ ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ደስ ያሰኘውን ሁሉ ያደርጋል።
7 እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያስነሣል፤መብረቅ ከዝናብ ጋር እንዲወርድ ያደርጋል፤ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል።
8 በኵር ሆኖ በግብፅ የተወለደውን፣ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ቀሠፈ።
9 ግብፅ ሆይ፤ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣በመካከልሽ ታምራትንና ድንቅን ሰደደ።