1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።
2 እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣በገናዎቻችንን ሰቀልን።
3 የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።
4 የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!
5 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ።