7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጥነህ መልስልኝ፤መንፈሴ ደከመች፤ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፣ፊትህን ከእኔ አትሰውር።
8 በአንተ ታምኛለሁና፣በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።
9 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መሰወሪያ አድርጌአለሁና፣ከጠላቶቼ አድነኝ።
10 አንተ አምላኬ ነህና፣ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ፤መልካሙ መንፈስህም፣በቀናችው መንገድ ይምራኝ።
11 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራ አውጣት።
12 ጠላቶቼንም ለእኔ ስላለህ ምሕረት ደምስሳቸው፤እኔ ባሪያህ ነኝና፣ነፍሴን የሚያስጨንቋትን ሁሉ አጥፋቸው።