13 እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፤ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአል።
14 በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል።
15 ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።
16 ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል።
17 የበረዶውን ድንጋይ ቍልቍል ይወረውረዋል፤በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን ሊቆም ይችላል?
18 ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈሳል።
19 ቃሉን ለያዕቆብ፣ሥርዐቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይገልጣል።