4 የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል።
5 ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ለጥበቡም ወሰን የለውም።
6 እግዚአብሔር ትሑታንን ከፍ ያደርጋል፤ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል።
7 ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።
8 ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።
9 ለእንስሳት ምግባቸውን፣የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።
10 እርሱ በፈረስ ኀይል አይደሰትም፤በሯጭም ብርታት ላይ ደስታውን አያደርግም።