1 ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ።
2 እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ።
3 ስሙን በሽብሰባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት።
4 እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።