17 ከኀያላን ጠላቶቼ አዳነኝ፤ከእኔ ከሚበረቱ ባላንጣዎቼም ታደገኝ።
18 እነርሱ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ።
19 ወደ ሰፊ ስፍራ አወጣኝ፤ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ።
20 እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መልሶልኛል፤እንደ እጄ ንጽሕናም ከፍሎኛል፤
21 የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም።
22 ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ሥርዐቱን ከፊቴ አላራቅሁም።
23 በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም፤ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።