21 የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም።
22 ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ሥርዐቱን ከፊቴ አላራቅሁም።
23 በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም፤ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።
24 እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መጠን፣በፊቱም እንደ እጄም ንጽሕና ከፍሎኛል።
25 ከታማኙ ጋር ታማኝ ትሆናለህ፤እንከን ከሌለበት ጋር ያለ እንከን ትሆናለህ፤
26 ከንጹሑ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ለጠማማው አንተ ትጠምበታለህ።
27 አንተ ትሑታንን ታድናለህ፤ትዕቢተኛውን ዐይን ግን ታዋርዳለህ።