29 በአንተ ጒልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ፤በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ።
30 የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው።መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ፣እርሱ ጋሻ ነው።
31 ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ?ከአምላካችንስ በቀር ዐምባ ማን ነው?
32 ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣መንገዴንም የሚያቃና እግዚአብሔር ነው።
33 እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤በከፍታዎችም ላይ ያቆመኛል።
34 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ክንዴም የናስ ቀስት መገተር ይችላል።
35 የድል ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፤ዝቅ ብለህም ከፍ አደረግኸኝ።