10 ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል።
11 ደግሞም አገልጋይህ በእርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው።
12 ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል?ከተሰወረ በደል አንጻኝ።
13 ባሪያህን ከድፍረት ኀጢአት ጠብቅ፤እንዳይሠለጥንብኝም ርዳኝ፤ያን ጊዜ ያለ እንከን እሆናለሁ፤ከታላቅ በደልም እነጻለሁ።
14 መጠጊያዬና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣በፊትህ ያማረ ይሁን።