1 ሕዝቦች ለምን ያሤራሉ?ሰዎችስ ለምን ከንቱ ነገር ያውጠነጥናሉ?
2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ፣ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤
3 “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፣የእግር ብረታቸውንም አውልቀን እንጣል” አሉ።
4 በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
5 ከዚያም በቊጣው ይናገራቸዋል፤በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል፤
6 ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል።
7 የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤