1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥ በኀይልህ ደስ ይለዋል፤በምትሰጠውም ድል እጅግ ሐሤት ያደርጋል።
2 የልቡን መሻት ሰጠኸው፤የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም። ሴላ
3 መልካም በረከት ይዘህ በመንገዱ ላይ ጠብቀኸው፤የንጹሕ ወርቅ ዘውድም በራሱ ላይ ደፋህለት።
4 ሕይወትን ለመነህ፤ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው።
5 ባቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ክብርንና ሞገስን አጐናጸፍኸው።