3 መልካም በረከት ይዘህ በመንገዱ ላይ ጠብቀኸው፤የንጹሕ ወርቅ ዘውድም በራሱ ላይ ደፋህለት።
4 ሕይወትን ለመነህ፤ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው።
5 ባቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ክብርንና ሞገስን አጐናጸፍኸው።
6 ዘላለማዊ በረከትን ሰጠኸው፤ከአንተ ዘንድ በሚገኝ ፍስሓም ደስ አሰኘኸው፤
7 ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፤ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ከቆመበት አይናወጥም።
8 እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፤ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ፈልጋ ትይዛለች።
9 በምትገለጥበት ጊዜ፣እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በመዓቱ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል፤እሳቱም ሙጥጥ አድርጋ ትበላቸዋለች።