3 ነፍሴንም ይመልሳታል።ስለ ስሙም፣በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።
4 በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ፤ብሄድ እንኳ፣አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ፣ክፉን አልፈራም፤በትርህና ምርኵዝህ፣እነርሱ ያጽናኑኛል።
5 ጠላቶቼ እያዩ፣በፊቴ ማዕድ አዘጋጀህልኝ፤ራሴን በዘይት ቀባህ፤ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል።
6 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣በጎነትና ምሕረት በእርግጥ ይከተሉኛል፤እኔም በእግዚአብሔር ቤት፣ለዘላለም እኖራለሁ።