2 እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፤በውሆችም ላይ አጽንቶአታል።
3 ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ሊወጣ ይችላል?በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
4 ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤በውሸት የማይምል፤
5 እርሱ በረከትን ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ምሕረትንም ከአዳኝ አምላኩ ይቀበላል።
6 እርሱን የሚፈልግ ትውልድ እንዲህ ነው፤የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ፊትህን የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው። ሴላ
7 እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤እናንተ የዘላለም በሮች፤የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
8 ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኀያል፤ እግዚአብሔር ነው በውጊያ ኀያል።