9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤መቼም ረዳቴ ነህና።አዳኝ አምላኬ ሆይ፤አትጣለኝ፤ አትተወኝም።
10 አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር ይቀበለኛል።
11 እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤ስለ ጠላቶቼም፣በቀና መንገድ ምራኝ።
12 ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ፤የሐሰት ምስክሮች ተነሥተውብኛልና፣ዐመፃ የሚረጩ ናቸው።
13 የእግዚአብሔርን ቸርነት፣በሕያዋን ምድር እንደማይ፣ሙሉ እምነቴ ነው።
14 እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤አይዞህ፣ በርታ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።