1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከታች አንሥተኸኛልና፣ጠላቶቼም በላዬ እንዳይደሰቱ አድርገሃልና፣ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
2 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ ጮኽሁ፤አንተም ፈወስኸኝ።
3 እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤ወደ ጒድጓድ ከመውረድም መልሰህ ሕያው አደረግኸኝ።
4 እናንተ ቅዱሳኑ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ቅዱስ ስሙንም አወድሱ።
5 ቊጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣በማለዳ ደስታ ይመጣል።
6 እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣“ከቶ አልናወጥም” አልሁ።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣ተራሮቼ ጸኑ፣ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣ውስጤ ታወከ።