3 እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤ወደ ጒድጓድ ከመውረድም መልሰህ ሕያው አደረግኸኝ።
4 እናንተ ቅዱሳኑ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ቅዱስ ስሙንም አወድሱ።
5 ቊጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣በማለዳ ደስታ ይመጣል።
6 እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣“ከቶ አልናወጥም” አልሁ።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣ተራሮቼ ጸኑ፣ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣ውስጤ ታወከ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤
9 “በእኔ ወደ ጒድጓድ መውረድ፣በመሞቴ ምን ጥቅም ይገኛል?ዐፈር ያመሰግንሃልን?ታማኝነትህንስ ይናገራልን?