1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ተተግኛለሁ፤እንግዲህ ዕፍረት ከቶ አይድረስብኝ፤በጽድቅህም ታደገኝ።
2 ጆሮህን ወደ እኔ መልሰህ ስማኝ፤ፈጥነህ አድነኝ፤መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ታድነኝም ዘንድ ምሽግ ሁነኝ።
3 አንተ ዐለቴና መጠጊያዬ ነህና፣ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤መንገዱንም ጠቍመኝ።
4 አንተ መጠጊያዬ ነህና፣በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ።
5 መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤አንተ ተቤዠኝ።
6 ለከንቱ ጣዖታት ስፍራ የሚሰጡትን ጠላሁ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ።