10 ሕይወቴ በመጨነቅ፣ዕድሜዬም በመቃተት ዐለቀ፤ከመከራዬ የተነሣ ጒልበት ከዳኝ፤ዐጥንቴም በውስጤ ሟሟ።
11 ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ፣ለጎረቤቶቼ መዘባበቻ፣ለወዳጆቼ መሣለቂያ ሆኛለሁ፤መንገድ ላይ የሚያገኙኝም ይሸሹኛል።
12 እንደ ሞተ ሰው ተረሳሁ፤እንደ ተሰበረ የሸክላ ዕቃም ተቈጠርሁ።
13 የብዙ ሰዎችን ሹክሹክታ እሰማለሁና፤ዙሪያው ሁሉ ሽብር አለ፤በእኔ ላይ ባሤሩ ጊዜ፣ሕይወቴን ለማጥፋት ዶለቱ።
14 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ፤“አንተ አምላኬ ነህ” እልሃለሁም።
15 ዘመኔ ያለው በእጅህ ነው፤ከጠላቶቼ እጅ ታደገኝ፤ከሚያሳድዱኝም አድነኝ።
16 ፊትህን በአገልጋይህ ላይ አብራ፤በምሕረትህም አድነኝ።