11 ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ፣ለጎረቤቶቼ መዘባበቻ፣ለወዳጆቼ መሣለቂያ ሆኛለሁ፤መንገድ ላይ የሚያገኙኝም ይሸሹኛል።
12 እንደ ሞተ ሰው ተረሳሁ፤እንደ ተሰበረ የሸክላ ዕቃም ተቈጠርሁ።
13 የብዙ ሰዎችን ሹክሹክታ እሰማለሁና፤ዙሪያው ሁሉ ሽብር አለ፤በእኔ ላይ ባሤሩ ጊዜ፣ሕይወቴን ለማጥፋት ዶለቱ።
14 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ፤“አንተ አምላኬ ነህ” እልሃለሁም።
15 ዘመኔ ያለው በእጅህ ነው፤ከጠላቶቼ እጅ ታደገኝ፤ከሚያሳድዱኝም አድነኝ።
16 ፊትህን በአገልጋይህ ላይ አብራ፤በምሕረትህም አድነኝ።
17 እግዚአብሔር ሆይ፤ወደ አንተ እጮኻለሁና አልፈር፤ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ሲኦል ገብተውም ጸጥ ይበሉ።