15 ዘመኔ ያለው በእጅህ ነው፤ከጠላቶቼ እጅ ታደገኝ፤ከሚያሳድዱኝም አድነኝ።
16 ፊትህን በአገልጋይህ ላይ አብራ፤በምሕረትህም አድነኝ።
17 እግዚአብሔር ሆይ፤ወደ አንተ እጮኻለሁና አልፈር፤ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ሲኦል ገብተውም ጸጥ ይበሉ።
18 በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ፣ትዕቢትንና ንቀትን የተሞሉ፣ዋሾ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።
19 በሰዎች ልጆች ፊት፣ለሚፈሩህ ያስቀመጥሃት፣መጠጊያ ላደረጉህም ያዘጋጀሃት፣በጎነትህ ምንኛ በዛች!
20 ከሰዎች ሤራ፣በማደሪያህ ውስጥ ትሸሽጋቸዋለህ፤ከአንደበት ጭቅጭቅም፣በድንኳንህ ውስጥ ትከልላቸዋለህ።
21 በተከበበች ከተማ ውስጥ፣የሚያስደንቅ ምሕረቱን ያሳየኝ፣ እግዚአብሔር ይባረክ።