2 ጆሮህን ወደ እኔ መልሰህ ስማኝ፤ፈጥነህ አድነኝ፤መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ታድነኝም ዘንድ ምሽግ ሁነኝ።
3 አንተ ዐለቴና መጠጊያዬ ነህና፣ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤መንገዱንም ጠቍመኝ።
4 አንተ መጠጊያዬ ነህና፣በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ።
5 መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤አንተ ተቤዠኝ።
6 ለከንቱ ጣዖታት ስፍራ የሚሰጡትን ጠላሁ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ።
7 በምሕረትህ ደስ እሰኛለሁ፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤መከራዬን አይተሃልና፤የነፍሴንም ጭንቀት ዐውቀሃል።
8 ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ነገር ግን እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው።