1 መተላለፉ ይቅር የተባለለት፣ኀጢአቱም የተሸፈነለት፣እንዴት ቡሩክ ነው!
2 እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው፣እርሱ ቡሩክ ነው።
3 ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ዝም ባልሁ ጊዜ፣ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤
4 በቀንና በሌሊት፣እጅህ ከብዳብኛለችና፤ኀይሌም የበጋ ትኵሳት እንደላሰው ነገር፣ከውስጤ ተሟጠጠ። ሴላ
5 ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤በደሌንም አልሸሸግሁም፤ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤አንተም የኀጢአቴን በደል፣ይቅር አልህ። ሴላ