1 ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ቅኖች ሊወድሱት ይገባቸዋል።
2 እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።
3 አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ።
4 የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነውና፤የሚሠራውም ሁሉ የታመነ ነው።
5 እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል፤ምድርም በምሕረቱ የተሞላች ናት።
6 በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት።