11 የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን ለዘላለም ይጸናል፤የልቡም ሐሳብ ለትውልድ ሁሉ ነው።
12 እግዚአብሔር አምላኩ የሆነው ሕዝብ፣ለርስቱ የመረጠውም ወገን የተባረከ ነው።
13 እግዚአብሔር ከሰማይ ይመለከታል፤የሰውንም ልጆች ሁሉ ያያል፤
14 ከማደሪያው ቦታ ሆኖ፣በምድር ወደሚኖሩት ሁሉ ይመለከታል፤
15 እርሱ የሁሉን ልብ የሠራ፣የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያስተውል ነው።
16 ንጉሥ በሰራዊቱ ታላቅነት አይድንም፤ጀግናም በኀይሉ ብርታት አያመልጥም።
17 በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤በብርቱ ጒልበቱም ማንንም አያድንም።