3 አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ።
4 የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነውና፤የሚሠራውም ሁሉ የታመነ ነው።
5 እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል፤ምድርም በምሕረቱ የተሞላች ናት።
6 በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት።
7 የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል።
8 ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።
9 እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤አዞአልና ጸኑም።