8 ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።
9 እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤አዞአልና ጸኑም።
10 እግዚአብሔር የሕዝቦችን ምክክር ከንቱ ያደርጋል፤የሕዝብንም ዕቅድ ያጨናግፋል።
11 የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን ለዘላለም ይጸናል፤የልቡም ሐሳብ ለትውልድ ሁሉ ነው።
12 እግዚአብሔር አምላኩ የሆነው ሕዝብ፣ለርስቱ የመረጠውም ወገን የተባረከ ነው።
13 እግዚአብሔር ከሰማይ ይመለከታል፤የሰውንም ልጆች ሁሉ ያያል፤
14 ከማደሪያው ቦታ ሆኖ፣በምድር ወደሚኖሩት ሁሉ ይመለከታል፤