19 የጻድቅ መከራው ብዙ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ከሁሉም ያድነዋል።
20 ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።
21 ኀጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል፤ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።
22 እግዚአብሔር የባሪያዎቹን ነፍስ ይቤዣል፤እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም።