7 እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤ያድናቸዋልም።
8 እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፤እርሱን መጠጊያ የሚያደርግ ምንኛ ቡሩክ ነው!
9 እናንተ ቅዱሳኑ፤ እግዚአብሔርን ፍሩት፤እርሱን የሚፈሩት አንዳች አያጡምና።
10 አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።
11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
12 ሕይወትን የሚወድ፣በጎውንም ያይ ዘንድ ዕድሜን የሚመኝ ማን ነው?
13 አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ።