1 ክፉውን ሰው፣በደል በልቡ ታናግረዋለች፤እግዚአብሔርን መፍራት፣በፊቱ የለም፤
2 በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና።
3 ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቶአል።
4 በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ክፋትንም አያርቅም።