5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል።
6 ጽድቅህ እንደ ታላላቅ ተራሮች፣ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰውንም እንስሳንም ታድናለህ።
7 አምላክ ሆይ፤ ምሕረትህ እንዴት ክቡር ነው!የሰዎች ልጆች ሁሉ፣በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ።
8 ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ።
9 የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤በብርሃንህም ብርሃንን እናያለን።
10 ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ ዘወትር አይቋረጥባቸው።
11 የትዕቢተኛ እግር በላዬ አይምጣ፤የክፉውም ሰው እጅ አያሳደኝ።