10 ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ስፍራውንም ብታስስ አታገኘውም።
11 ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።
12 ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል።
13 እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፤ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና።
14 ድኾችንና ችግረኞችን ለመጣል፣አካሄዳቸው ቀና የሆነውንም ለመግደል፣ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤ቀስታቸውንም ገተሩ።
15 ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ቀስታቸውም ይሰበራል።
16 የጻድቅ ጥቂት ሀብት፣ከክፉዎች ብዙ ጥሪት ይበልጣል።