2 እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፤እንደ ለምለም ቅጠልም ይጠወልጋሉ።
3 በእግዚአብሔር ታመን፤ መልካምንም አድርግ፤በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ዘና ብለህ ተሰማራ።
4 በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
5 መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤በእርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤
6 ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣ያንተን ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል።
7 በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤መንገዱ በተቃናለት፣ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።
8 ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ።