22 እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤እርሱ የሚረግማቸው ግን ይጠፋሉ።
23 የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይጸናል፤በመንገዱ ደስ ይለዋል።
24 ቢሰናከልም አይወድቅም፤ እግዚአብሔር በእጁ ደግፎ ይይዘዋልና።
25 ጐልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ፤ነገር ግን ጻድቅ ሲጣል፣ዘሩም እንጀራ ሲለምን አላየሁም።
26 ሁል ጊዜ ቸር ነው፤ ያበድራልም፤ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ።
27 ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፤ለዘላለምም ትኖራለህ።
28 እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳልና፤ታማኞቹንም አይጥልም፤ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፤የኀጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል።