30 የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤አንደበቱም ፍትሐዊ ነገር ያወራል።
31 የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤አካሄዱም አይወላገድም።
32 ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤ሊገድሉትም ይሻሉ።
33 እግዚአብሔር ግን በእጃቸው አይጥለውም፤ፍርድ ፊት ሲቀርብም አሳልፎ አይሰጠውም።
34 እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፤መንገዱንም ጠብቅ፤ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።
35 ክፉና ጨካኙን ሰው፣እንደ ሊባኖስ ዝግባ ለምልሞ አየሁት፤
36 ዳግመኛ በዚያ ሳልፍ፣ እነሆ፣ በቦታው አልነበረም፤ብፈልገውም አልተገኘም።