5 መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤በእርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤
6 ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣ያንተን ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል።
7 በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤መንገዱ በተቃናለት፣ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።
8 ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ።
9 ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።
10 ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ስፍራውንም ብታስስ አታገኘውም።
11 ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።