12 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ።
13 እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቈሮ፣አፉንም መክፈት እንደማይችል ዲዳ ሆንሁ።
14 በእርግጥም ጆሮው እንደማይሰማ፣አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ።
15 እግዚአብሔር ሆይ፤ በተስፋ እጠብቅሃለሁ፤ጌታ አምላኬ ሆይ፤ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ።
16 እኔ፣ “ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ አይበላቸው፤እግሬም ሲንሸራተት፣ በላዬ አይኵራሩብኝ” ብያለሁና።
17 ልወድቅ ተቃርቤአለሁ፤ከሥቃዬም ከቶ አልተላቀቅሁም።
18 በደሌን እናዘዛለሁ፤ኀጢአቴም አውካኛለች።