2 ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና፤እጅህም ተጭናኛለች።
3 ከቍጣህ የተነሣ ሰውነቴ ጤና አጥቶአል፤ከኀጢአቴም የተነሣ ዐጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።
4 በደሌ ውጦኛል፤እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል።
5 ከንዝህላልነቴ የተነሣ፣ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤
6 ዐንገቴን ደፋሁ፤ ጐበጥሁም፤ቀኑንም ሙሉ በትካዜ ተመላለስሁ።
7 ወገቤ እንደ እሳት ነዶአል፤ሰውነቴም ጤና የለውም።
8 እጅግ ዝያለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤ከልቤም መታወክ የተነሣ እጮኻለሁ።