1 እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣መንገዴን እጠብቃለሁ፤ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ።
2 እንደ ዲዳ ዝም አልሁ፤ለበጎ ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ሆኖም ጭንቀቴ ባሰ።
3 ልቤ በውስጤ ጋለ፤በማሰላስልበትም ጊዜ እሳቱ ነደደ፤ከዚያም በአንደበቴ እንዲህ ተናገርሁ፤
4 “እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።