3 ልቤ በውስጤ ጋለ፤በማሰላስልበትም ጊዜ እሳቱ ነደደ፤ከዚያም በአንደበቴ እንዲህ ተናገርሁ፤
4 “እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።
5 እነሆ፤ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አስቀመጥህ፤ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፤በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ተን ነው። ሴላ
6 ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤በከንቱም ይታወካል፤ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል።
7 “ጌታ ሆይ፤ አሁንስ ወደ ማን ልመልከት?ተስፋዬ በአንተ ላይ ነው።
8 ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤የሰነፎች መሣለቂያ አታድርገኝ።
9 ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም።