5 እነሆ፤ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አስቀመጥህ፤ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፤በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ተን ነው። ሴላ
6 ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤በከንቱም ይታወካል፤ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል።
7 “ጌታ ሆይ፤ አሁንስ ወደ ማን ልመልከት?ተስፋዬ በአንተ ላይ ነው።
8 ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤የሰነፎች መሣለቂያ አታድርገኝ።
9 ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም።
10 ክንድህን አንሣልኝ፤ከእጅህ ምት የተነሣ ደክሜአለሁና።
11 ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤በእርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ