1 የጽድቄ አምላክ ሆይ፤በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።
2 ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅ ታደርጋላችሁ?እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? ሐሰትንስ ትሻላችሁ? ሴላ
3 እግዚአብሔር ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፤ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።
4 ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ
5 የጽድቅን መሥዋዕት አቅርቡ፤ በእግዚአብሔርም ታመኑ።