4 ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ
5 የጽድቅን መሥዋዕት አቅርቡ፤ በእግዚአብሔርም ታመኑ።
6 ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል? ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።
7 ስንዴና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ባመረቱ ጊዜ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ፣አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል።
8 በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።