1 ለድኾች የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው፤እርሱንም እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል።
2 እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል፤በምድርም ላይ ይባርከዋል፤ለጠላቶቹም ምኞትም አሳልፎ አይሰጠውም።
3 ታሞ ባለበት ዐልጋ ላይ እግዚአብሔር ይንከባከበዋል፤በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል።
4 እኔም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረት አድርግልኝ፤አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።