5 ጠላቶቼ በክፋት በመናገር፣ “የሚሞተው መቼ ነው? ስሙስየሚደመሰሰው ምን ቀን ነው?” ይላሉ።
6 ሊጠይቀኝ የሚመጣ ቢኖር፣በልቡ ስድብ እያጠራቀመ፣ ከዐንገት በላይ ይናገራል፤ወጥቶም ወሬ ይነዛል።
7 ጠላቶቼ ሁሉ ግንባር ፈጥረው ይንሾካሾኩብኛል፤እንዲህ እያሉም፣የከፋ ነገር በላዬ ያውጠነጥናሉ፤
8 “ክፉ ደዌ ይዞታል፤ከእንግዲህም ከተኛበት አይነሣም።”
9 እንጀራዬን ተካፍሎኝ የበላ፣የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።
10 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ምሕረት አድርግልኝ፤የእጃቸውን እንድከፍላቸው አስነሣኝ።
11 ጠላቴ በላዬ ድል አላገኘምና፣እንደ ወደድኸኝ በዚህ አወቅሁ።