6 ሊጠይቀኝ የሚመጣ ቢኖር፣በልቡ ስድብ እያጠራቀመ፣ ከዐንገት በላይ ይናገራል፤ወጥቶም ወሬ ይነዛል።
7 ጠላቶቼ ሁሉ ግንባር ፈጥረው ይንሾካሾኩብኛል፤እንዲህ እያሉም፣የከፋ ነገር በላዬ ያውጠነጥናሉ፤
8 “ክፉ ደዌ ይዞታል፤ከእንግዲህም ከተኛበት አይነሣም።”
9 እንጀራዬን ተካፍሎኝ የበላ፣የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።
10 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ምሕረት አድርግልኝ፤የእጃቸውን እንድከፍላቸው አስነሣኝ።
11 ጠላቴ በላዬ ድል አላገኘምና፣እንደ ወደድኸኝ በዚህ አወቅሁ።
12 ስለ ጭንቀቴ ደግፈህ ይዘኸኛል፤በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።