6 በቀስቴ አልተማመንም፤ሰይፌም አያስጥለኝም።
7 አንተ ግን በጠላቶቻችን ላይ ድልን ትሰጠናለህ፤ባላንጣዎቻችንንም ታሳፍራለህ።
8 ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን። ሴላ
9 አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም።
10 ከጠላት ፊት እንድናፈገፍግ አደረግኸን፤ባላንጣዎቻችንም ዘረፉን።
11 እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤በሕዝቦችም መካከል በተንኸን።
12 ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም።