8 ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን። ሴላ
9 አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም።
10 ከጠላት ፊት እንድናፈገፍግ አደረግኸን፤ባላንጣዎቻችንም ዘረፉን።
11 እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤በሕዝቦችም መካከል በተንኸን።
12 ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም።
13 ለጎረቤቶቻችን ስድብ፣በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።
14 በሕዝቦች ዘንድ መተረቻ፣በሰዎች መካከል በንቀት ራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።