2 በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ የሆነው ንጉሥ፣ልዑል እግዚአብሔር የሚያስፈራ ነውና።
3 ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን።
4 ለሚወደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን፣ርስታችንን እርሱ መረጠልን። ሴላ
5 አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።
6 አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤
7 እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ምርጥ ዝማሬ አቅርቡለት።
8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሦአል፤እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል።